በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የብልፅግና ፓርቲ የመሰረታዊ ድርጅት አባላት ኮንፈረንስ መድረክ በዛሬዉ ዕለት ተካሂዷል ።
የዕለቱን መርሐ ግብር በማስመልከት በንግግር የከፈቱት የቢሮው የመሰረታዊ ድርጅት ም/ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ኻሊድ አብዲ እንዳሉት የፓርቲው ዕሳቤ ፣ ዓላማና ዕሴት የተላበሰ አባላት መኖር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል ።
የዛሬው መድረክ ዓላማ የቢሮው የብልፅግና ፓርቲ መሰረታዊ ድርጅት የ2016 በጀት አመት አፈጻጸም ጠንካራ እና ደካማ ሂደቶች በመገምገም በቀጣይም የነበሩትን ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እንዲሁም የታዩትን ድክመቶች በማረም የተሻለ ሥራለመሰራት ታሳቢ ሆኖ እንደተዘጋጀም ተናግረዋል ።
በኮንፈረንሱ ላይ የመሰረታዊ ድርጅት መተዳደሪያ ደንብ እና የብልፅግና ፓርቲ መሰረተዊ ድርጅት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም ላይ ወይይት በማካሄድ ሪፖርቱ ፀድቋል።
በመጨረሻም በየመሰረታዊ ፓርቲ አመራሮችና ህዋስ አባላት በማፅደቅ መድረኩ ተጠናቋል።










