ክቡር አቶ ሐምዲ ሰላሐዲን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ!
የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮን በበላይነት እንዲመሩ ክቡር አቶ ሐምዲ ሰላሐዲን የቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።
አዲሱ አመራር የክልሉን የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት፣ የመልካም አስተዳደርና የሀብት አጠቃቀም ሥርዓቱን ለማጠናከር እንዲሁም የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ዳር ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቃል።
የቢሮው አመራሮችና መላው ሠራተኞች ለክቡር አቶ ሐምዲ ሰላሐዲን ላገኙት ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት የተሰማቸውን ልባዊ ደስታ እየገለጹ፤ አዲሱ የኃላፊነት ዘመን የሕዝባችንን አጠቃላይ የልማትና የዕድገት ተስፋዎች የሚያሳካ፣ የስኬትና የውጤት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ይመኛሉ።
የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ






