በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የሚመራ የክልሉ ገቢ አሰባሳብ አብይ ኮሚቴ የ2017 በጀት አመት የሐምሌ ወር የገቢ እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ።
ውይይቱም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ በአቶ መሐመድ ያህያ ሰብሳቢነት የገቢዎች ቢሮ፤ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፤ የሐረር ማዘጋጃ ቤት እና የፕላንና ልማት ኮሚሽን በተገኙበት በቀረበው የ2017 በጀት አመት የሐምሌ ወር የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም ላይ በስፋት እና በጥልቀት ተወያይተዋል ።
የ2017 በጀት ዓመት የሀምሌ ወር የገቢ ዕቅድ 233.7 ሚሊየን ሲሆን አፈጻጸሙ 181.17 ሚሊየን ወይም 78 በመቶ አፈጻጸም የተመዘገበ መሆኑን በገቢዎች ባለስልጣን የቀረበ ሪፖርት ያመለክታል ።
በክልሉ ያለውን የገቢ አቅም አሟጦ በመሰብሰብ መልሶ ለክልሉ ልማት ለማዋል የተቀናጀ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ሊኖር እንደሚገባም ተገልጿል።
በገቢ አሰባሰብ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል።
በሌላ በኩል በክልል ደረጃ የደረቅ ቁሻሻ አሰባሰብና አወጋገድን በተመለከተ የሀኪም ወረዳ ከአካባቢው ማህበረሰብ እና በወረዳው አገልግሎት በሚሰጡባቸው ቦታዎች ገቢ በመሰብሰብ ቁሻሻዎቹን ማስወገድ በሚቻልበት ሁኔታ በፓይለት ደረጃ ለመጀመር ታሳቢ ተደርጎ ውሳኔ እንዲሰጥበት በቀረበው ሀሳብ ላይ በመወያየት ሀኪም ወረዳ የደረቅ ቆሻሻ ገቢ እንዲሰበስቡ ውሳኔ አስተላልፈዋል






